የመከላከያ ጠቅላይ መምሪያ ጠቅላላ አገልግሎት የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ የሰራዊት አባላት ማዕረግ አለበሰ

የካቲት 3/2014 (ዋልታ) የመከላከያ ጠቅላይ መምሪያ ጠቅላላ አገልግሎት ዋና ዳይሬክቶሬት በስራ አፈጻፀማቸው የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ የሰራዊት አባላት ማዕረግ አልብሷል፡፡

የተሰጣቸውን ተልዕኮ በብቃት ለተወጡ የሰራዊት አባላትም የሜዳልያ ሸልማት እና ሰርተፍኬት እንደተበረከተላቸው የመከላከያ ሰራዊቱ መረጃ አመልክቷል፡፡

የዋና ዳይሬክቶሬቱ ዳይሬክተር ሜ/ጀነራል ታደሰ መኩሪያ፤ የሽብር ቡድኑ ትሕነግ በሰራዊታችን ላይ ድንገተኛ ጥቃት ከፈጸመ ጀምሮ በንጹኃን ለይ በርካታ ግፎችን ማድረሱን አስታውሰው፤ በዋና ዳይሬክቶሬቱ ስር የሚገኙ ሁሉም ክፍሎች በእልህ እና በወኔ በመነሳሳት እስከ ግምባር ድረስ ለሰራዊቱ የሚያስፈልገውን ተተኳሸ እና ሁለንተናዊ ጠቅላላ አገልግሎት በማቅረብ ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል ብለዋል፡፡

የማዕረግ ተሿሚዎቹ እና የሜዳልያ ተሸላሚዎቹ በቀጣይ የሚሰጣቸውን ግዳጅ እና ተልዕኮ በብቃት ለመወጣት መነሳሳት እና አቅም እንደፈጠረላቸው ተናግረዋል፡፡