የመገናኛ ብዙሀን በተፋሰስ ልማትና አካባቢ ጥበቃ ስራዎች ላይ ትኩረት ሰጥተው ሊሰሩ እንደሚገባ ተገለፀ

ሰኔ 25/2013 (ዋልታ) – የመገናኛ ብዙሀን በተፋሰስ ልማትና አካባቢ ጥበቃ ስራዎች ላይ ትኩረት ሰጥተው ሊሰሩ እንደሚገባ ተገለፀ፡፡

የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ህዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሄራዊ ም/ቤት ፅ/ቤት ከተፋሰስ ልማት ባለስልጣን ከአካባቢ የደንና የአየር ንብረት ለውጥ ኮሚሽን እና ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመሬትና ውሀ ሀብት ማዕከል ጋር በመተባበር በቢሾፍቱ ከተማ ለመገናኛ ብዙሀን ባለሙያዎች ስልጠና እየሰጠ ይገኛል።
በስልጠና መርሀ ግብሩ ላይ የመገናኛ ብዙሀን በተፋሰስ ልማትና አካባቢ ጥበቃ ስራዎች ላይ አትኩረው መስራታቸው ለሀገር የሚኖረው ጥቅም የጎላ እንደሆነ ተጠቁሟል።
በመድረኩ የተፈጥሮ ሀብት መጎዳት ለበርካታ ችግሮች ስለሚያጋልጥ አካባቢያችንን በመጠበቅ የተፋሰስ ስራዎችን ለማረጋገጥ ሊሰራ ይገባል ተብሏል።
የተፈጥሮ ሀብት ስራ ከዘመቻ በዘለለ ባህል ሆኖ እንዲቀጥል መሰራት እንዳለበት ተመላክቷል።
(በሱራፌል መንግስቴ እና ሳሙኤል ሀጎስ)