የማዕድን ዘርፍ ለምጣኔ ሃብታዊ ዕድገት ያለውን አስተዋጽኦ ለማሳደግ ስምምነት ተፈረመ

የካቲት 25/2014 (ዋልታ) የማዕድን ዘርፍ ለአገር ምጣኔ ሃብታዊ ዕድገት እያደረገ ያለውን አስተዋጽኦ በዘመናዊ መልክ ለማሳደግ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና ማዕድን ሚኒስቴር አብሮ ለመሥራት የሚያስችል ስምምነት ተፈራረሙ፡፡
በባህላዊ ዘዴ በሚመረት የወርቅ ማዕድን ዙሪያ ባሉ ችግሮች ላይ ጥናት በማድረግ ማዕድኑን ለአገር ኢኮኖሚያዊ ዕድገት እያደረገ ያለውን አስተዋጽኦ በዘመናዊ መልክ ለማሳደግ የተፈረመ የውል ስምምነት እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡
ስምምነቱን የማዕድን ሚኒስትር ታከለ ኡማ እና የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ጣሰው ወልደሃና (ፕ/ር) ተፈራርመዋል፡፡
ከማዕድን ሚኒስትር ታከለ ኡማ ማኅበራዊ የትስስር ገጽ የተገኘው መረጃ እንደሚያሳየው ስምምነቱም ዩኒቨርሲቲው በባህላዊ መልክ የሚደረጉትን የማዕድን ማውጣት ሥራን በዘመናዊ መልክ አቀላጥፎ ለመሥራት እንዲያስችል የተለያዩ ጥናትና ምርምር በዘመናዊ መልክ አካሂዶ ለሚኒስቴሩ ያስረክባል።