የምርጫ ሂደቱን ለመከታተል ታዛቢዎች ወደ ኢትዮጵያ እየገቡ ነው

ሰኔ 11/2013 (ዋልታ) – ጥቂት ቀናቶች የቀረውን ሀገራዊ ምርጫ ሂደት ለመከታተል ታዛቢዎች ወደ ኢትዮጵያ እየገቡ ይገኛሉ።

ትላንት ማምሻውን የቀድሞው የናይጄሪያ ኘሬዝዳንት የነበሩት በአሁኑ ወቅት ደግሞ በአፍሪካ ህብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድን ሀላፊ የሆኑት ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ  አዲስ አበባ መግባታቸውን ከሰላም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የሰላም ሚኒስቴር ዴኤታ ፍሬዓለም ሺባባው ለሃላፊው አቀባበል አድርገውላቸዋል።