የሩስያ ፌዴሬሽን ሴናተር አንድሬ ኤ ክሊሞቭ ለሶስት ቀናት ይፋዊ የስራ ጉብኝት ነገ አዲስ አበባ ይገባሉ፡፡
የከፍተኛ ሴናተሩ ጉብኝትም ሩሲያ ከኢትዮጵያ እና ከሌሎች የአፍሪካ አገራት ጋር የፖለቲካ ትብብርን ለማጠናከር የሚረዳ ነው፡፡
የሴናተሩ ጉብኝት ከኢትዮጵያ ጋር ብቻ ሳይሆን ከሌሎች የአፍሪካ መንግስታት የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ጠንካራ ግንኙነት ለመፍጠር የሚያስችል መድረክ የሚፈጥር መሆኑን በኢትዮጵያ የሩሲያ ኤንበሲ አስታውቋል።
ኢትዮጵያ እና ሩሲያ ባለፉት ጥቂት ዓመታት በተለያዩ ደረጃዎች ከፍተኛ የሆነ የፖለቲካ ግንኙነት እንዳላቸውም ኤንባሲው ገልጿል፡፡
የሴናተሩ ጉብኝት ዓላማም በኢትዮጵያ እና በሩሲያ መካከል ያለውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር የታሰበ እንደሆነ ከኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የተገኘው መረጃ አመላክቷል።