የሪፐብሊክ ጥበቃ ሃይል በጠላት ላይ እርምጃ እየወሰደ መሆኑ ተገለጸ

ነሃሴ 05/2013 (ዋልታ) – የሪፐብሊኩ ጥበቃ ሃይል ከአጋር ሃይሎች ጋር  በጠላት ላይ የማያዳግም እርምጃ እየወሰደ ይገኛል፡፡

በዚህም 35 የአሸባሪ ቡድን አባላት የተማረኩ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ ከ18 አመት በታች የሚሆኑ 20 ህፃናት ሲሆኑ 15ቱ ደግሞ ከ18 እስከ 25 ዓመት መሆናቸውን ለማረጋገጥ መቻሉ ተነግሯል፡፡

የምስራቅ ዕዝ ዘመቻ ሃላፊ ኮሎኔል ጉደታ ኦፍጋአ የጁንታው አሸባሪ ሃይል በአፋር ክልል ጭፍራ ግንባር በኩል የመጣውን የጁንታው አሸባሪ ቡድን ከሪፐብሊኩ ጥበቃ ሃይል እንዲሁም ከልዩ ዘመቻ ጋር በመሆን ድባቅ መመታቱን አረጋግጠዋል፡፡

የኢትዮጵያ ህዝብ አሸባሪው በሚያስራጨው የሃሰት ወሬ መደናበር እንደለሌበተም ማሳሰባቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡

በተጨባጭ የሚወራው እና በተግባር የሚታየው በምንም  መልኩ አይገናኝም ያሉት ኮሎኔል ጉደታ ስለሆነም  ህዝባችን አንድነቱን በማጠናከር ለሰራዊቱ እያደረገው ያለውን ድጋፍ በማጠናከር መቀጠል አለበት ብለዋል፡፡

ከተማረኩ የጁንታው የሽብር ቡድን አባላት መካከል ለትሽ ሃድጉ ጁንታው በማስገደድ ወደ ወጊያ እንዳስገባት እና በሷ እድሜ ክልል ከ18 አመት በታች በርካታ ህፃናትን በማስገደድ እና በማስገባት ትግራይን ያለ ወጣት እያስቀራት መሆኑን ተናግራለች፡፡

ሸዊት ፍትዊ  የተባለው በበኩሉየጁንታው አሸባሪ ቡድን ከመንገድ ላይ አፍሶ ወደ ውጊያ በግድ እንዳስገባቸው ነው የሚናገረው፡፡

ከተማረኩኝ በኋላ እነሱ ካሉት በተቃራኒ የመከላከያ ሰራዊታችን በእንክብካቤ በማከም ምግብ እና ውሃ በመስጠት ነፍሴን ታድጎኛል ብሏል፡፡