የሰላም ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል በኢትዮጵያ ከጃፓን አምባሳደር ኢቶ ታካኮ ጋር ተወያዩ

ጃፓን በትግራይ ክልል ከተካሄደው የህግ ማስከበር ዘመቻ ጋር በተያያዘ የሰብአዊ ድጋፍና መልሶ የማቋቋም ሂደቱን ለመደገፍ ዝግጁ መሆኗን በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር ኢቶ ታካኮን ተናገሩ፡፡

የሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል በኢትዮጵያ ከጃፓን አምባሳደር ኢቶ ታካኮ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡

በዚህ ወቅትም ሚኒስትሯ በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል የተካሄደውን የህግ ማስከበር ሂደት በተመለከተ ገለጻ አድርገዋል፡፡

በዚህም በትግራይ ክልል እየተካሄደ ስላለው የሰብዓዊ ድጋፍና ክልሉን መልሶ ለማቋቋም እየተከናወኑ ያሉ ተግባራትን በተመለከተ ለአምባሳደሯ ገልጸውላቸዋል፡፡

አምባሳደር ታካኮ በበኩላቸው ጃፓን በቀውስ ጊዜ ስራ አስተዳደር ሰፊ ልምድ ያላት ሀገር መሆኗን ጠቅሰዋል፡፡

ከዚህ ጋር ተያይዞም የሰብዓዊ ድጋፍና መልሶ ማቋቋም ሂደቱን አስፈላጊ በሆነ መስክ ሁሉ ለመደገፍ መንግስታቸው ያለውን ፍላጎትና ዝግጁነት መግለጻቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡