የሰሜን ዕዝ በአሸባሪው ህወሓት ከጀርባው የተወጋበት 1ኛ ዓመት እየታሰበ ነው


ጥቅምት 24/2014 (ዋልታ)
በአሸባሪው ሕወሓት የአገር ክህደት ጥቃት ሰማዕት የሆኑ የመከላከያ ሰራዊት አባላት እየታሰቡ ነው፡፡
በአዲስ አበባ ጦር ኃይሎች እየተካሄደ ባለው የመታሰቢያ መርሃ ግብር ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት ተገኝተዋል፡፡
በመርሃ ግብሩ የሻማ ማብራትና የህሊና ፀሎት ማድረግ ስነ ስርዓት ተፈፀሟል፡፡
ኢትዮጵያዊያን የጥቅምት 24 ሰማዕታት መታሰቢያ መርሃ ግብሮችን የህሊና ጸሎት ማድረግን ጨምሮ ለሰራዊቱ ያላቸውን ድጋፍ በሚገልፁ የተለያዩ ሁነቶች ዛሬ ዕለቱን እያሰቡት ነው፡፡
ከእነዚህ ውስጥ በርካቶች በየአቅራቢያቸው ባለ የደም ባንክና ጊዜያዊ የደም መስጫ ማዕከላት የሚሳተፉበት የደም ልገሳ ሂደት አንዱ ነው፡፡
ጥቅምት 24/2013 ሌሊት የሽብር ቡድኑ ሕወሓት ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ ሕዝብን ሲጠብቅ በነበረው የመከላከያ ሰራዊት የሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት በመሰንዘር አገር የማፍረስ ጦርነት የከፈተበት ዕለት ሲሆን፤ በኢትዮጵያዊያን ላይ ክህደት የፈፀመበት ታሪክ የማይዘነጋው ድርጊት ሆኖም ይታሰባል፡፡