የሰርጌ ላቭሮቭ በኢትዮጵያ ያደረጉት ቆይታ ፍሬያማ እንደነበር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ

ሐምሌ 21/2014 (ዋልታ) የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ በኢትዮጵያ ያደረጉት ቆይታ በጣም አጭር ቢሆንም ፍሬያማ ነበር ሲል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።

የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አምባሳደር መለሰ አለም ከሚኒስትሩ ጋር በተደረገ ውይይት ከሶቬዬት ሕብረት ጀምሮ ሲንከባለል የነበረ የ162 ሚሊዮን ዶላር ብድር ወደ ልማት እንዲዞር ከስምምነት ተደርሷል ብለዋል።

መንግስት ወደ ፈለገው ልማት እንዲዞር ተስማምተናል ያሉት አምባሳደሩ ለመልካዋከና ሀይል ማመንጫ፣ ለባልቻ ሆስፒታልና መሰል ተቋማትን ለማሳደግ ይውላል ብለዋል።

በሌላም በኩል የውጭ ሀገር ዜጎች ሕጋዊነት ምዝገባ ከተጀመረ በኋላ 60 ሺሕ የሚሆኑ የውጭ ሀገር ዜጎች መመዝገባቸው ገልጸዋል።

ምዝገባው የሚደረገው ሕጋዊነት  ለማረጋገጥ እና ማግኘት የሚገባቸውን ጥቅም ማግኘት እንዲችሉ ነው ተብሏል።

ምዝገባው የተከናወነው ለዚሁ ተግባር ተብሎ በተቋቋሙ 121 ቅርንጫፍ ጣብያዎች ሲሆን በአዲስ አበባና በዙርያዋ ባሉ አካባቢዎች ምዝገባ ተካሂዷል፤ በቀጣይም በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች ይከናወናል ተብሏል።

ምዝገባው ቪዛቸውን ሳያድሱ የሚኖሩ ዜጎችን ወደ ሕጋዊነት ለማምጣት ይረዳል ተብሏል።

በመስከረም ቸርነት