የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር ስልጣን ለቀቁ

የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር

ታኅሣሥ 25/2014 (ዋልታ) የሰዳን ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክ ስልጣን መልቀቃቸውን አስታወቁ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለሱዳን ሕዝብ ባስተላለፉት መልዕክት ስልጣን መልቀቃቸውን ይፋ አድርገዋል።

ሱዳን በቅርቡ ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት ማድረጓን ተከትሎ በፖለቲካ ቀውስ ውስጥ ስትሆን መፈንቅለ መንግስት ያደረገው ወታደራዊ ኃይሉ አስሯቸው የነበረውን ጠቅላይ ሚኒስትር ሀምዶክ ከእስር ፈቶ ወደ ስልጣን ቢመልሳቸውም የዚያች ሀገር የፖለቲካ ቀውስም ሆነ ሕዝባዊ ተቃውሞ ጋብ ማለት አልቻለም።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከወታደራዊ መሪው አል ቡርሃን ጋር የደረሱት ስምምነት በሲቪሉ የፖለቲካ ስብስብ ዘንድ አልተወደደም።

በመጨረሻም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሱዳን ፖለቲካ ላይ ተፅእኖ ማድረግ እንደተሳናቸው እና የገቡትን ቃል መጠበቅ ባለመቻላቸው ስልጣን ለመልቀቅ መገደዳቸውን ተናግረዋል።