የስኩል ኦፍ ኔሽን ትምህርት ቤት መታገድ

ጳጉሜ 03/2013 (ዋልታ) ትምህርት ሚኒስቴር የዓለም አቀፍና የማህበረሰብ ትምህርት ቤቶች ፈቃድ አሰጣጥና ዕድሳት መመሪያን መሰረት አድርጎ ስኩል ኦፍ ኔሽን ትምህርት ቤት ላይ እገዳ መጣሉን አስታውቋል፡፡

አዲሱ የትምህርት ዘመን ከመጀመሩ በፊት በትምህርት ክፍያ ጭማሪ ዙሪያ በተደጋጋሚ ከወላጆች ቅሬታ በመቅረቡ የትምህርት ሚኒስቴር የዘርፍ አመራሮችና የባለሙያዎች ቡድን ትምህርት ቤቱንና የወላጅ ኮሚቴውን በማወያየት ከስምምነት ላይ እንዲደርሱ በተደጋጋሚ ጊዜ ድጋፍ ሲያደርግ ቆይቷል ነው የተባለው፡፡

ቢሆንም በተደረጉት ውይይቶች ስምምነት ላይ መድረስ ባለመቻሉ ትምህርት ቤቱ ከዛሬ ጀምሮ ትምህርት ሚኒስቴር ባወጣው መመሪያ መሰረት ከወላጅ ኮሚቴ ጋር ፈጥኖ በመነጋገር ምንም አይነት የትምህርት ስራ እንዳይሰራ መታገዱን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡