የሶማሌ ክልል ምክር መደበኛ ጉባዔ እያካሄ ነው

ሐምሌ 23/2014 (ዋልታ) የሶማሌ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 3ኛ ዓመት 2ኛ መደበኛ ጉባዔ እያካሄ ነው፡፡

ከዛሬ ጀምሮ ለሶስት ተከታታይ ቀናት በሚካሄደው ጉባኤ በክልሉ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በልማት፣ በሰላምና በመልካም አስተዳደር ዙሪያ የተከናወኑ ተግባራት አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ በምክር ቤቱ አባላት ውይይት ይደረግበታል ተብሏል፡፡

እንዲሁም በክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤትና ዋና ኦዴተር መስሪያ ቤት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት እንደሚካሄድበት ይጠበቃል።

ምክር ቤቱ ውይይት ከሚያደረግባቸው ዘጠኝ አጀንዳዎች መካከል የ2015 ዓ.ም በጀት ላይ ተወያይቶ ያፀድቃልም መባሉን የዚዜአ ዘገባ አመላክቷል።