የቀዳማዊት እመቤት ጽ/ቤት በጅማ በሚያስገነባው ት/ቤት 5 ሺሕ ችግኝ ተተከለ

ሰኔ 7/2014 (ዋልታ) 85 ከመቶ ግንባታው በተጠናቀቀውና የቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት በጅማ ዞን አኮ ከተማ በሚያስገነባው ትምህርት ቤት 5 ሺሕ ችግኝ ተተከለ፡፡

የአካባቢው ነዋሪዎች፣ መምህራንና ተማሪዎች በጋራ ችግኞቹን በትምህርት ቤቱና በዙሪያው ተክለዋል፡፡

ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቱ በተያዘው ዓመት ግንባታው ተጠናቆ ለ2015 ዓ.ም ትምህርት መስጠት የሚጀምር መሆኑን የቀዳማዊት እመቤት ጽ/ቤት መረጃ ያሳያል፡፡