የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ አዲስ አበባ ሲገባ ደማቅ አቀባበል ተደረገለት

ሰኔ 25/2014 (ዋልታ) የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ ዋንጫውን ይዞ አዲስ አበባ ሲገባ ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል።

ለ15ኛ ጊዜ የፕሪምየር ሊጉን ዋንጫ ያነሱት ቅዱስ ጊዮርጊሶች ቦሌ ዓለም ዐቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ የክለቡ ሥራ አስኪያጅ አብነት ገብረ መስቀልን ጨምሮ የክለቡ አመራሮች እና በርካታ የክለቡ ደጋፊዎች ተገኝተው አቀባበል አድርገዋል።

የቡድኑ ተጫዋቾች እና ደጋፊዎች ዋንጫውን በክፍት መኪና ይዘው በአዲስ አበባ ዋና ዋና ጎዳናዎች ላይ በመዘዋወር ደስታቸውን እያከበሩ ይገኛሉ።

ቅዱስ ጊዮርጊስ በ30ኛ ሳምንት የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አዲስ አበባ ከተማን 4 ለ 0 አሸንፎ በ65 ነጥብ ሻምፒዮን መሆኑ ይታወሳል።

በመሠረት ተስፋዬ