የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት 12ኛ መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀመረ

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት

ሐምሌ 15/2013 (ዋልታ) – የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት የ5ኛ ዓመት 6ኛ የሥራ ዘመን 12ኛ መደበኛ ጉባኤውን ዛሬ ማካሄድ ጀምሯል።

ምክር ቤቱ ለሁለት ቀናት የሚቆውን ጉባዔውን የውይይት አጀንዳዎችን እንዲሁም የ11ኛውን መደበኛ እና 6ኛ አስቸኳይ ጉባኤ ቃለ-ጉባኤ መርምሮ በማጽደቅ መጀመሩን የክልሉ መንግሥት የኮሙዩኒኬሽን ጽህፈት ቤት መረጃ አመልክቷል።

በዛሬ የጉባዔ ውሎ በርዕሰ-መስተዳድሩ የሚቀርበውን የክልሉ መንግሥት የ2013 በጀት ዓመት አፈጻጸም በማድመጥ መርምሮ እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል፡፡

ምክር ቤቱ በክልሉም ሆነ በመላው ሀገሪቱ በተፈጠሩ የተለያዩ የፀጥታ ችግሮች ለደረሰው የሰው ሕይወት መጥፋት እና መፈናቀል የሕሊና ጸሎት በማድረግ ነው ጉባዔውን ማካሄድ መጀመሩ ነው የተገለጸው።