የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት አስቸኳይ ጉባዔውን እያካሄደ ነው

የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት 6ኛ የሥራ ዘመን 6ኛ አስቸኳይ ጉባዔውን እካሄደ ነው ፡፡

ምክር ቤቱ በመተከል ዞን በተፈጠረው የጸጥታ ችግር ህይወታቸውን ላጡ እና ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች የህሊና ጸሎት በማድረግ  ነው ጉባዔውን ማካሄድ  የጀመረው።

ምክር ቤቱ በአስቸኳይ ጉባዔው ከመተከል ዞን የጸጥታ ችግር ጋር በተያያዘ የተጠረጠሩ የምክር ቤት አባላትን ያለመከሰስ መብት ያነሳል ተብሎም እንደሚጠበቅም  የቤንሻንጉል ጉምዝ የመንግስት  ኮሙኒኬሽን  የተገኘው መረጃ  ያመላክታል፡፡