የብላቴ ኮማንዶና አየር ወለድ ኃይል ማሰልጠኛ ማዕከል እና ደቡብ ፖሊስ የችግኝ ተከላ አካሄዱ

ሐምሌ 5/2014 (ዋልታ) የብላቴ ኮማንዶና አየር ወለድ ኃይል ማሰልጠኛ ማዕከል ከደቡብ ፖሊስ እና ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር በመሆን አረንጓዴ አሻራ ማሳረፍ የሚያስችል የችግኝ ተከላ አካሄዱ፡፡

የችግኝ ተከላ መርሐ ግብሩን ያስጀመሩት የደቡብ ከልል ርዕሰ መስተዳደር እርስቱ ይርዳ የጀግኖች መፍለቂያ በሆነው የልዩ ኃይል ማሠልጠኛ ተገኝቼ ከሠራዊታችን ጋር ችግኝ ስተክል ትልቅ ክብርና ኩራት ተሰምቶኛል ብለዋል፡፡

የማሰልጠኛ ማዕከሉ ዋና አዛዥ ኮሎኔል ቦጃ አጋ እንዳሉት 4 ሺሕ ችግኞችን ተክለን መጪው ትውልድ እንዲጠቅም አሻራችንን እናስቀምጣለን ያሉ ሲሆን የተተከሉ ችግኞችን ለመንከባከብም አደረጃጀት ፈጥረናል ማለታቸውን የመከላከያ ሠራዊት መረጃ ያመላክታል።