የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ነገ መደበኛ ስብሰባውን ማካሄድ ይጀምራል

የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ነገ መደበኛ ስብሰባውን ማካሄድ ይጀምራል፡፡
የፓርቲው ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ከነገ አርብ ህዳር 25 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ በመደበኛ ስብሰባው በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ይመክራል፡፡
ኮሚቴው በተለያዩ ወቅታዊና አገራዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ አቅጣጫ ያስቀምጣል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።