የብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ አዲስ አበባ ከሚኖሩ የትግራይ ተወላጅ ወጣቶች ጋር ውይይት እያደረገ ነው

የብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ አዲስ አበባ ከሚኖሩ የትግራይ ተወላጅ ወጣቶች ጋር ውይይት እያደረገ ነው፡፡

ወጣቶቹ በወቅታዊ የሀገሪቷ ጉዳይ ላይ ውይይት እንዲያደርጉ ታስቦ የተዘጋጀ መድረክ እንደሆነ የብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ስመኝ አድነው ለዋልታ ቴሌቪዥን ተናግረዋል፡፡

ኃላፊው ወጣቶቹ በመድረኩ ላይ አሁን ክልሉ ያለበትን ወቅታዊ ሁኔታ ላይ እና በቀጣይ ጉዳይ ላይ ያተኮረ ሃሳብ እንደሚያነሱ ይጠበቃል ብለዋል፡፡

ፅንፈኛው የህወሃት ቡድን በሀገር እና በሀገር መከላከያ ሰራዊት ላይ የፈፀመውን ክህደት በመውገዝ መንገግስት የጀመረውን ህግ የማስከበር ስራ እና መልሶ ግንባታ ሃሳብን በመረዳት ሁሉም የክልሉ ወጣቶች ከመንግስት ጎን እንዲሰለፉ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡

በቀጣይ በክልሉ የተለያዩ አምስት ከተሞች በመገኘት በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከክልሉ አዲሱ ጊዜያዊ አስተዳደር ጋር በመሆን እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡ በመድረኩ ላይ በከተማዋ የሚኖሩ ከ500 ያላነሱ ወጣቶች እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡

(በሚልኪያስ አዱኛ)