የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት ጅግጅጋ ገቡ

ነሐሴ 20/2014 (ዋልታ) በብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ የተመራ የፌደራል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ልዑክ ዛሬ ጅግጅጋ ገቡ።

ለልዑኩ የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት ሙስጠፋ ሙሁመድ እና ሌሎች የክልሉ አመራሮች ደማቅ አቀባበል አድርገዋል።

የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህን ጨምሮ የፌዴራልና የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች የተለያዩ በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ የተከናወኑ የልማት ሥራዎችን እንደሚጎበኙ የክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን መረጃ ያመለክታል።