የብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ ለመከላከያ ሰራዊት ድጋፍ አደረገ

መሰከረም 23/2014 (ዋልታ) የመተከል ዞን እና የፓዊ ወረዳ የብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ ለመከላከያ ሰራዊት የተለያዩ የደረቅ ስንቅ ድጋፍ አድርገዋል፡፡
የተዘጋጀውን ደረቅ ስንቅ የተረከቡት በስፍራው የሚገኝ የሰራዊት ክፍል ምክትል አዛዥ ለአፕሬሽናል ኮሎኔል መልካሙ በየነ የመተከል ዞን ሴቶች ለሰራዊቱ እያደረጉ ላለው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።
የመተከል ዞን ብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ አስተባባሪ ወይዘሮ ነገሪ ፉፋ ለመተከል ዞን ሕዝብ ሰላም ለሚተጋው የመከላከያ ሰራዊት ድጋፍ ተጠናክሮ ይቀጥላል ማለታቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡