የብሔራዊ ባንክ ገዥ ከዓለም የገንዘብ ድርጅት የሥራ ኃላፊዎች ጋር ተወያዩ

ጥቅምት 3/2015 (ዋልታ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ይናገር ደሴ ከዓለም የገንዘብ ድርጅት የሞነተሪና ካፒታል ማርኬት ዲፓርትመንት ምክትል ዳይሬክተርና ሌሎች የሥራ ኃላፊዎች ጋር ተወያዩ።

በዚህም በዲፓርትመንቱና በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መካከል በውጭ ምንዛሬ፣ በገንዘብ ገበያ፣ በዲጂታል ገንዘብ፣ በውጭ ባንኮች ሬጉሌሽንና ሱፐርቪዥን እንዲሁም በኢንሹራንስ ዘርፍ ሬጉሌሽን ረገድ በትብብር መሥራት በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ ተወያይተዋል።

በተጨማሪም አስፈላጊው የቴክኒክ ድጋፍ ስለሚሰጥበት እና በቀጣይ የሥራ ሂደቶች ላይ መግባባት ላይ መድረሳቸውን በአሜሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW