የብሔራዊ የሳይበር ደህንነት ወር ከጥቅምት 1-30 ይካሄዳል

መስከረም 27/2014 (ዋልታ) – ብሔራዊ የሳይበር ደህንነት ወር በኢትዮጵያ ለ2ኛ ጊዜ በአለም አቀፍ ደረጃ ለ18ኛ ጊዜ ከጥቅምት 1 እስከ ጥቅምት 30 እንደሚካሄድ የኢንፎርሜሽንና መረብ ደህንነት ኤጀንሲ አስታውቋል፡፡

የኤጀንሲው ዋና ዳሬክተር ሹመት ግዛው (ዶ/ር) “ጥቅምት የአለም የሳይበር ደህንነት ወር” በሚል እንደሚከበር ገልጸው፣ ሀገራት የዜጎቻቸውን እንዲሁም የተቋማቶቻቸውን የሳይበር ደህንነት ንቃት ለመገንባት እንደሚያስችላቸው ተናግረዋል፡፡

ሀገርን ከሳይበር ጥቃት ለመታደግ የሁሉም ባለድርሻ አካላት ሚና ወሳኝ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ወሩ ተነሳሽነትን በሚጨምሩ እንዲሁም ክህሎትን በሚያክሉ ሁነቶች እንደሚከበር ተገልጿል፡፡

መርኃግብሩ በመጪው ሰኞ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት የሚጀመር ነውም ተብሏል፡፡