የብረታ ብረት እና ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪዎች በኢትዮጵያ እየተስፋፉ ነው – ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ

ታኅሣሥ 26/2015 (ዋልታ) የብረታ ብረት እና ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪዎች በኢትዮጵያ እየተስፋፉ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናገሩ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከአዲስ አበባ 30 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ገላን ከተማ ያለው ቢኬ ብረታ ብረት ኢንጂነሪንግ ኮምፕሌክስ ከባድ መኪኖችን፣ አውቶብሶችን በመገጣጠም እና የተለያዩ የኢንዱስትሪ ግብዐቶችን በማምረት ላይ ነው ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ባለሃብቶች በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል።