የተቀናጀ የጭነት ትራንስፖርት ማስተዳደሪያ ሥርዓት ይፋ ሆነ

ታኅሣሥ 21/2014 (ዋልታ) የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር የተቀናጀ የጭነት ትራንስፖርት ማስተዳደሪያ ሥርዓትን በዛሬው ዕለት ይፋ አድርጓል።

ሥርዓቱ ደንበኞች ባሉበት ቦታ ሆነው አዲስ ፍቃድ ማውጣት፣ ዓመታዊ ፍቃድ ማደስ፣ አዳዲስ ተሽከርካሪዎችን ማስመዝገብ፣ የጉዞ መርሃ ግብርን ማሳወቅ፣ የድንበር ተሻጋሪ መታወቂያዎችን መስጠት እና የተሽከርካሪዎችን የጉዞ ርቀትና ጭነት ማሳወቅ የሚያስችል ነው ተብሏል።

በመርሃ ግብሩ የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስትር ዳግማዊት ሞገስን ጨምሮ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር)፣ የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ ዳይሬክተር የሹመት ግዛው (ዶ/ር) እና የተለያዩ ጥሪ የተደረገላቸው የስራ ኃላፊዎች መገኘታቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡

የገቢና ወጪ ጭነቶችን በማጓጓዝ ረገድ የተሽከርካሪ ድርሻ 90 ከመቶ በላይ የያዘ መሆኑም ተጠቁሟል፡፡

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት፦
የአማርኛ ፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ ይከተሉ
ከአረብኛ ፌስቡክ ገፃችን ጋርም ይጓዙ
የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
የትዊተር ገፃችንን ይከተሉ
አብራችሁን ስለሆናችሁ ደስተኞች ነን