የታላቁ ህዳሴ ግድብ ዋንጫ በሐረማያ ከተማ ደማቅ አቀባበል ተደረገለት

ግንቦት 10/2014 (ዋልታ) የታላቁ ህዳሴ ግድብ ዋንጫ በምስራቅ ሀረርጌ ዞን ሐረማያ ከተማ በዞኑ ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም የከተማዋ ዋሪዎች ደማቅ አቀባበል አድርገውለታል።

ምስራቅ ሀረርጌ ዞን የሐረማያ ከተማ አስተዳደር ዋናጫውን ከኦሮሚያ ክልል ሰበታ ከተማ ነው የተረከበው።
የምስራቅ ሀረርጌ ዞን አስተዳዳሪ ሚስኪ መሀመድ የታላቁ ህዳሴ ግድብ የሀገሪቱን ምርትና ምርታማነት በማሳደግ ከፍተኛ አበርክቶ ይኖረዋል ብለዋል።

አያይዘውም ግድቡ ከውጭ ሀገራት ድጋፍ ሳይፈልግ በሀገር ውስጥ ወጪው የተሸፈነ መሆኑ አንስተዋል።

የህዳሴ ግድቡ የአንድነታችን ማሳያ ሀገራችን በዓለም መድረክ ከፍ ብላ እንድትታይ ያደረገ ነው።

በመሆኑ አሁንም ሁሉም የኅብረተሰብ ክፍል ለህዳሴ ግድቡ በስኬት መጥናቀቅ እስካሁን ሲያደርገው እንደነበረው ሁሉ በአሁኑ ወቅትም ቦንድ በመግዛት ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።

የታላቁ የህዳሴ ግድብ ዋንጫ በምስራቅ ሀረርጌ ለአንድ ሳምንት በሚኖረው ቆይታ 30 ሚሊየን ብር ለመሰብሰብ መታቀዱ ተገልጿል።

በመርኃ ግብሩ ላይ የቦንድ ሽያጭ በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡

ተስፋዬ ኃይሉ (ከሐረማያ)