የታላቁ አንዋር መስጅድ ምክትል ኢማም ሸይኽ ሁሴን አሊ አረፉ

ሸይኽ ሁሴን አሊ

ሚያዝያ 12/2013 (ዋልታ) – የታላቁ አንዋር መስጅድ ምክትል ኢማም እና ኡስታዝ የነበሩት ሸይኽ ሐጅ ሁሴን አሊ በ63 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፡፡

በሰሜን ወሎ ሐራ በተባለ አካባቢ የተወለዱት ሸይኽ ሁሴን አሊ ከልጅነታቸው ጀምሮ በበርካታ የእስልምና ሊቆች እስላማዊ ትምህርት ተምረዋል።

የቀብር ስነ ስርዓቱም በነገው ዕለት በታላቁ አንዋር መስጅድ ከጠዋቱ አራት ስዓት ጀምሮ ታላላቅ ኡለማዎች፣ ከፍተኛ የመንግሥት ኃላፊዎች እና የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በተገኙበት በኮልፌ ሙስሊም መካነ መቃብር ይፈጸማል፡፡

ሸይኽ ሁሴን አሊ ባለትዳር እና የሦስት ልጆች አባት እንደነበሩም ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡