የታንዛኒያ ፕሬዝዳንት ሳሚያ ሱሉሉ ሀሰን አዲስ አበባ ገቡ

የታንዛኒያ ፕሬዝዳንት ሳሚያ ሱሉሉ ሀሰን

የካቲት 9/2015 (ዋልታ) የመጀመሪያዋ ሴት የታንዛኒያ ፕሬዝዳንት ሳሚያ ሱሉሉ ሀሰን በአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገቡ።

ለምስራቅ አፍሪካ ማህበረሰብ የመጀመሪያ ሴት መሪ የሆኑት ፕሬዘዳንቷ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ፕሬዝዳንቷ “የአፍሪካ አህጉራዊ የንግድ ቀጣና ትግበራን ማፋጠን” በሚል መሪ ሃሳብ በሚካሄደው 36ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ይሳተፋሉ ነው የተባለው።

ፕሬዝዳንቷ በሞት የተለዩት ጆን ማጉፉሊን ተክተው የታንዛኒያ ፕሬዘዳንት መሆናቸው ይታወቃል።

በደረሰ አማረ