የታይም መጽሔት የዓመቱ ታዳጊ ትውልደ ኢትዮጵያዊው ተመራማሪ

ትውልደ ኢትዮጵያዊው ሄማን በቀለ በቆዳ ካንሰር ላይ በሚያደርገው የምርምር ሥራ የታይም መጽሔት የዓመቱ የላቀ ተጽዕኖ ፈጣሪ ታዳጊ ተብሎ ተሰይሟል።

ታዳጊ ሄማን በቀለ የቆዳ ካንሰርን የሚከላከል እና በተመጣጣኝ ዋጋ ለገበያ ይቀርባል የተባለ ሳሙና ለመስራት ምርምር እያደረገ ይገኛል።

በአሜሪካ ቨርጂኒያ የሚኖረው የ15 ዓመቱ ትውልደ ኢትዮጵዊው ታዳጊ ሄማን ታይም መጽሔት ከ8 እስከ 16 ዓመት ዕድሜ ያሉ የላቀ አስተዋፅኦ ያላቸውን ልጆች በሚመርጥበት በዚህ መርኃ ግብር የዓመቱ ታዳጊ (TIME’s 2024 Kid of the Year) ሆኖ ተመርጧል፡፡

“እኔ ያደረኩትን ማንም ሰው ማድረግ ይችላል” ሲል ለታይም መጽሔት የተናገረው ታዳጊው ተመራማሪ “አንድ ሀሳብ አመጣሁ። በሀሳቡ ላይ ሰራሁ፤ ወደ ተግባር መቀየርም ችያለሁ” ብሏል።

በ4 ዓመቱ ከኢትዮጵያ ወደ አሜሪካ የተጓዘው ሄማን ከዚህ ቀደም “የአሜሪካ ወጣቱ ምርጥ ተመራማሪ” ተብሎ እንዲሁም ሌሎች ሽልማቶችን አግኝቷል።