የትምህርት ሚኒስቴር ያዘጋጀው የኮቪድ-19 ፕሮቶኮል

ትምህርት ሚኒስቴር

ጳጉሜ 1/2013 (ዋልታ) የትምህርት ሚኒስቴር በ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የትምህርት አሰጣጡ እንዴት መሆን እንዳለበት ከጤና ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የኮቪድ-19 ፕሮቶኮል ማዘጋጀቱን አስታወቀ፡፡

ሚኒስቴሩ በ2013 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ባስቀመጠው የኮቪድ-19 ፕሮቶኮል መሰረት ትምህርት በቀንና ፈረቃ ሲሰጥ መቆየቱ ተገልጿል፡፡

በ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የትምህርት አሰጣጡ እንዴት መሆን እንዳለበት ደግሞ ከጤና ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የኮቪድ19 ፕሮቶኮል እንዳዘጋጀም ጠቁሟል።

በዚህም በ2014 ዓ.ም በሚኖረው የመደበኛ ትምህርት አሰጣጥ ሂደት ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት እንደሚካሄድ ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።