የትንሳኤ በዓል በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ እየተከበረ ነው

ሚያዝያ 16/2014 (ዋልታ) የትንሳኤ በዓል በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ እየተከበረ ይገኛል።
ፋሲካን በማስመልከት የሃይማኖት አባቶች ባስተላለፉት መልዕክት “የኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓልን ስናከብር አንድነታችንን በማጠናከር እና የኢትዮጵያን ዘላቂ ሠላም ለማስፈን በተግባር በመስራት ሊሆን ይገባል” ነው ያሉት፡፡
“የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ የሰው ልጅ ሃጥያት የተሰረየበት፣ ፍቅር የተገኘበት እንዲሁም ደኅንነት የተጎናፀፈበት ነው” ብለዋል፡፡
በዓሉን በተለያየ ምክንያት ለችግር የተጋለጡ ወገኖችን በመደገፍ እና በመንከባከብ ማሳለፍ እንደሚገባም የሃይማኖት አባቶቹ አሳስበዋል፡፡
ሕዝበ ክርስቲያኑም በመላ ሀገሪቱ ሠላም እንዲሰፍን ጥረቱን እንዲያጠናክር ጠይቀዋል፡፡