የቻይና ማዕድን ኩባንያዎች በኢትዮጵያ እንዲሳተፉ መግባባት ላይ ተደረሰ

መጋቢት 30/2014 (ዋልታ) አዳዲስ የቻይና ማዕድን ኩባንያዎች በኢትዮጵያ የማዕድን ዘርፍ ላይ እንዲሳተፉ ለማድረግ መግባባት ላይ ተደረሰ፡፡
የማዕድን ሚኒስትር ታከለ ዑማ በኢትዮጵያ ከቻይና አምባሳደር ዣው ዢዋን ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡
ከቻይና አምባሳደር ዣው ዢዋን ጋር በኢትዮጵያ በማዕድን ዘርፍ ላይ የተሰማሩ የቻይና ኩባንያዎች ተሳትፎን ለማጠንከርና አዳዲስ የቻይና ማዕድን ኩባንያዎች በኢትዮጵያ የማዕድን ዘርፍ ላይ እንዲሳተፉ ለማድረግ የሚያስችል ውይይት ማድረጋቸውን ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡
በዚህም በጋራ ለመስራት ከአምባሳደሩ ጋር መግባባታቸውንም ገልጸዋል፡፡