የነዳጅ ምርቶች መሸጫ ዋጋ እስከ መጋቢት 30 ባለበት እንደሚቀጥል ተገለጸ

የካቲት 21/2014 (ዋልታ) ከየካቲት 19 እስከ መጋቢት 30 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ ከቀላል ጥቁር ናፍታ፣ ከባድ ጥቁር ናፍታና ከአውሮፕላን ነዳጅ በስተቀር የሌሎች የነዳጅ ምርቶች ዋጋ ባለበት እንዲቀጥል ተወሰነ፡፡

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የነዳጅ ምርቶች መሸጫ ዋጋን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ በየዓመቱ ከ3 ቢሊየን ዶላር በላይ እየወጣ የሚቀርበው የነዳጅ ምርት የአጠቃቀምና የግብይት ሂደት ላይ ሰፊ ችግሮች የሚስተዋሉበት መሆኑን አመልክቷል።

ሚኒስቴሩ ይህን ሁኔታ ለማስተካከል ኅብረተሰቡ ምርቱን በከፍተኛ ቁጠባ የመጠቀምና የግል አሽከርካሪዎችም ተሽከርካሪዎቻቸውን በተመጣጠነ አኳሃን በማንቀሳቀስ ብዙኃን ትራንስፖርትን የመጠቀም ልምድ ሊያዳብሩ እንደሚገባ ገልጿል፡፡

ሁሉም የኅብረተሰብ ክፍል በነዳጅ ምርት የሚፈፀሙ ህገወጥ የነዳጅ ምርት ዝውውርና ኮንትሮባንድ ተግባራት በመጠቆምና በማጋለጥ በየደረጃው ካለው የፀጥታ አካል ጋር ሊሠራ ይገባል ብሏል፡፡

በቀጣይም በዓለም ገበያ የሚኖረው የነዳጅ ዋጋ መነሻ በማድረግ እንደአስፈላጊነቱ ማስተካከያ ሊደረግ የሚችል መሆኑን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW
ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth
ዩቲዩብ https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured
ቲዊተር https://twitter.com/walta_info
አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን!