የንግድ ባንክ የ10ኛ ዙር ይቆጥቡ ይሸለሙ መርኃግብር ዕጣ ወጣ

የካቲት 25/2014 (ዋልታ) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የ10ኛ ዙር ይቆጥቡ ይሸለሙ መርኃ ግብር የዕጣ አወጣጥ ስነሥርዓት አካሄደ፡፡

መርኃ-ግብሩ ከ30 ሚሊዮን ደምበኞች በላይ የተሳተፉበት ሲሆን 72 ደምበኞች እድለኛ ሆነዋል።

በዚህም በአንደኛ እጣ 2 አፖርትመንት፣ በ2ኛ እጣ 10 ዘመናዊ የቤት አውቶሞቢሎች፣ በ3ኛ እጣ 30 ባለሦሥት እግር ተሽከርካሪዎች እንዲሁም በ4ኛ እጣ 30 ላፕቶፖች ለባለእድለኛ ቆጣቢዎች በሽልማት ተበርክተዋል፡፡

በሀኒ አበበ