የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን “አሚኮ ኅብር” የተሰኘ አዲስ ቻናል የማስጀመሪያ ሥነ ሥርዓት እየተካሄደ ነው

“አሚኮ ኅብር”

ሰኔ 13/2014 (ዋልታ) የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን “አሚኮ ኅብር” የተሰኘ አዲስ ቻናል የማስጀመሪያ ሥነ ሥርዓት እየተካሄደ ነው፡፡

ቻናሉ በ10 ቋንቋዎች መደበኛ ሥርጭቱን የሚጀምር ሲሆን አማርኛ፣ ኦሮምኛ፣ ትግርኛ፣ አፋርኛ፣ ኽምጣና፣ ጉምዝኛ፣ አዊኛ፡ እንግሊዝኛ እና በአረብኛ ቋንቋዎች ይገኙበታል፡፡

በማስጀመሪያ ሥነ ሠርዓቱ ላይ የአማራ ክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ/ር)፣ የመገንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) እንዲሁም የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች እና ታዋቂ ግለሰቦች ተገኝተዋል።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW