የአማራ ክልል ልዩ ኃይል አዛዥ የነበሩት ብ/ጄኔራል ተፈራ የርዕሰ መሥተዳደሩ አማካሪ ሆነው ተመደቡ

የካቲት 10/2014 (ዋልታ) የአማራ ክልል መንግሥት በፀጥታ ዘርፍ የአመራር ምደባና ስምሪት ማስተካከያ ማድረጉን ተከትሎ የክልሉ ልዩ ኃይል አዛዥ የነበሩት ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ የርዕሰ መሥተዳደሩ አማካሪ ሆነው ተመደቡ።

ክልሉ የገጠመው የሰላምና የፀጥታ ችግሮችን በአግባቡ ለመቅረፍ ያስችል ዘንድ በክልሉ ያሉ የፀጥታ መዋቅሩ ላይ ያሉ ጉድለቶችን እና ጥንካሬዎችን በዝርዝር መገምገሙን ክልሉ አስታውቋል።

ክልሉ የገጠመውን የኅልውና አደጋ በአግባቡ በመመከት የሕዝቡን የፀጥታ ስጋት ለመቀነስ የአመራር ምደባና ስምሪት ማስተካከያው አስፈልጓል ነው የተባለው።

ይህን ተከትሎ ወበዚህምው የልዩ ኃይል አዛዥ የነበሩት ብርጋዴ ጄኔራል ተፈራ ማሞ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር የፀጥታ አማካሪ ሲደረጉ፤ የሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ የነበሩት ሜጀር ጄኔራል መሠለ በለጠ የልዩ ኃይል ዋና አዛዥ ሆነው መሾማቸው ነው የተገለፀው።