የአማራ ክልል የቀድሞው ፖሊስ ኮሚሽነር አበረ አዳሙ የቀብር ስነ ስርዓት ተፈፀመ

የአማራ ክልል የቀድሞው ፖሊስ ኮሚሽነር አበረ አዳሙ

ሚያዝያ 28/2013 (ዋልታ) – የአማራ ክልል የቀድሞው ፖሊስ ኮሚሽነር አበረ አዳሙ የቀብር ስነ ስርዓት በባህር ዳር ፈለገ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ ካቴድራል ቤተክርስቲያን ተፈፀመ፡፡

የቀብር ስነ-ስርዓታቸው የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ አመራሮች፣ የሀገር መከላከያ ሰራዊት፣ የክልሉ ከፍተኛ የፖሊስ መኮንኖችና አባላት፣ ወዳጅ ዘመዶቻቸውና ቤተሰቦቻቸው በተገኙበት ነው የተፈፀመው፡፡

አቶ አበረ በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር በመሆን ከየካቲት 2011 ዓ.ም እስከ ሚያዝያ 2013 ዓ.ም ድረስ አገልግለዋል፡፡

አቶ አበረ አዳሙ ባጋጠማችው ድንገተኛ ህመም ሚያዝያ 26 ቀን 2013 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ይታወሳል፡፡

የአማራ ክልል የቀድሞው ፖሊስ ኮሚሽነር አቶ አበረ አዳሙ ባለትዳርና የሁለት ወንድ ልጆች አባት እንደነበሩ ከአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡