የአረፋ በዓል በወራቤ ከተማ እየተከበረ ነው

ሐምሌ 13/2013 (ዋልታ) – 1442ኛው  የኢድ አልአድሃ አረፋ በዓል በስልጤ ዞን ወራቤ ከተማ እየተከበረ ነው።

በዓሉ ከማለዳው  ጀምሮ በኢድ ተክቢራ እና በሰላት  እየተከበረ ነው።

ለበዓሉ ታዳሚዎች የእንኳን አደረሳቹህ መልእክት ያስተላለፋት የወራቤ ከተማ ከንቲባ አቶ ናስር ጀማል  አረፋን የህዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የውሃ ሙሌት በተጠናቀቀበት ማግስት በማከበራችን የተለየ ደስታ ፈጥአሮብናል ብለዋል።

ሃገር  በጁንታው ጥቃት ተቃቶባታል ያሉት ከንቲባው ሙስሊሙ ከመከላከያ ጎን በመቆምና ተገቢውን ድጋፍ በማድረግ ሃገር የማዳን ግዴታውን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል።

ለዋልታ አስተያየታቸውን የሰጡ የበዓሉ ታዳሚዎች ህዳሴ ግድብን አናጠናቅቃለለን ከመከላከያ ጎን በመቆም ሀገአራችንን እንታደጋለን ብለዋል።