የአርሲ ዞን ነዋሪዎች ለሀገር መከላከያ ሰራዊት የድጋፍ ሰልፍ አደረጉ

ለአገር መከላከያ ሰራዊት ድጋፍ ሰልፍ

ሐምሌ 18/2013 (ዋልታ) – የአሰላ ከተማ እና አርሲ ዞን ነዋሪዎች ለሀገር መከላከያ ሰራዊት የድጋፍ ሰልፍ አደረጉ።

ከዞኑና ከከተማ አስተዳደሩ 2 ሺህ 608 ሀገር ወዳድ ወጣቶች መከላከያን ለመቀላቀል መዘጋጀታቸው ተገልጿል።

ከዚህ በፊት 600 በላይ የአርሲ ዞን ነዋሪዎች ለመከላከያ ሰራዊት ያበረከተ ሲሆን፣ አሁንም ከ700 በላይ ማበርከቱን የአሰላ ከተማ ከንቲባ አቶ ገብሬ ኡርጌሶ ገልፀዋል፡፡

(በነሞምሳ አድሱ)