የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ከ6ሕ በላይ ተማሪዎችን እያስመረቀ ነው

የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ

መስከረም 29/2014 (ዋልታ) የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ከ6 ሺሕ የበላይ ተማሪዎችን በአባያ ካምፓስ እያስመረቀ ይገኛል።

ዩኒቨርሲቲው በ1976 ዓ.ም ከተጀመረ ጀምሮ በውሃ ምህንድስና በርካታ ምሁራንን ማፍራቱ ይታወቃል።

ከ1996 ዓ.ም ጀምሮ በምህንድስና፣ ጤና፣ ግብርና፣ ቢዝነስ፣ በተፈጥሮ እና በቀመር ሳይንስ ተማሪዎችን ተቀብሎ ሲያስተምር ቆይቷል።

ዩኒቨርሲቲው በዋናው ግቢ፣ ነጭ ሳር፣ ዓባያ፣ ጫሞና ኩልፎ ካምፓሶች የሚገኙ የ2013 ዓ.ም ተመራቂ ተማሪዎችን በዛሬው እለት በዓባያ ካምፓስ ሲያስመርቅ የሳውላ ካምፓስ ተማሪዎችን ደግሞ በነገው እለት መስከረም 30 በሳውላ ያስመርቃል።

በቁምነገር አህመድ