የአሸባሪው ሕወሓት ወረራ ከ41 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርትን አሳጣ

ኅዳር 3/2014(ዋልታ) አሸባሪው ሕወሓት በፈጸመው ወረራ ከ41 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት መታጣቱን የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ አስታወቀ፡፡

ቢሮ በሽብርተኛው የትግራይ ወራሪ ኃይል የወደመውን ሰብል ለመተካት በሚያስችሉ ሁኔታዎች ላይ በክልሉ ከሚገኙ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንቶች ጋር ውይይት አድርጓል።

የሽብር ቡድኑ ወረራ በፈጸመባቸው ዞኖች 2 ሚሊዮን ሄክታር መሬት ሰብል ወድሟል።

በዚህም ከ6 ነጥብ 3 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ለችግር መጋለጡን ነው ቢሮው ያስታወቀው፡፡

የቢሮው ኃላፊ አልማዝ ጊዜው (ደ/ር) በወረራው ምክንያት ደግሞ 266 ቢሊዮን ብር የሚገመት ሃብት መውደሙን ገልጸዋል።

በግብርና ዘርፉ ላይ የደረሰውን ውድመት በፍጥነት መልሶ ለማቋቋም ወቅቱን የጠበቀና የተፋጠነ የሰብል ልማት ሥራን በበልግ፣ በቅብብሎሽ እና በቀሪ እርጥበት 498 ሺሕ ሄክታር መሬት በመሸፈን ከ14 ሚሊዮን በላይ ኩንታል ምርት ማምረት ቀዳሚ ተግባር መሆኑ አንስተዋል።
ለዚህም 8 ነጥብ 9 ቢሊዮን ብር እንደሚያስፈልግ ነው የቢሮ ኃላፊዋ ያስታወቁት።