የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ከተማ አቀፍ የምርጫ ቅስቀሳ አካሄደ

የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ

ሚያዝያ 29/2013 (ዋልታ) – የአዲስ አበባ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ከተማ አቀፍ የምርጫ ቅስቀሳውን አካሂዷል፡፡

በቅስቀሳ መርኃግብሩ የከተማ አስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤን ጨምሮ ፓርቲው በአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤትና ለፌደራል ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያቀረባቸው ዕጩዎች ተገኝተው በጋራ በመሆን የምርጫ ቅስቀሳውን አድርገዋል፡፡

ፓርቲው የይምረጡኝ የመኪና ላይ ቅስቀሳውን ከመስቀል አደባባይ መነሻውን በማድረግ በመላው አዲስ አበባ ከተማ እንደሚያደረግ ተመላክቷል፡፡

(በሰለሞን በየነ)