የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የሙሉቀን ሀፍቱን (ዶ/ር) የህግ ከለላ አነሳ

ሐምሌ 8/2014 (ዋልታ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ያለመከሰስ መብት ያላቸውን የምክር ቤቱ አባል የሙሉቀን ሀፍቱን (ዶ/ር) የህግ ከለላ በአብላጫ ድምፅ አንስቷል።

የአዲስ አበባ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ኃላፊ የሆኑት ሙሉቀን ሀፍቱን (ዶ/ር) የህግ ከለላ የፍትህ ሚኒስቴር ባቀረበው ጥያቄ መሰረት ምክር ቤቱ በ93 ድጋፍ እና በ6 ድምፀ ተአቅቦ ያለመከሰስ መብቱ እንዲነሳ በአብላጫ ድምፅ ወስኗል።

የህግ ይነሳልን ጥያቄው ከቤቶች እጣ አወጣጥ ጋር የተያያዘ መሆኑን የምክር ቤቱ አፈጉባኤ ቡዜና አልቃድር ፍትህ ሚኒስትርን ደብዳቤ ለምክር ቤቱ ባቀረቡበት ወቅት መናገራቸውን የከንቲባ ጽሕፈት ቤት መረጃ አመላክቷል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ለሁለት ቀናት የሚያካሂደውን 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 3ኛ እና የበጀት ዓመቱ ማጠቃለያ ጉባኤውን ጀምሯል።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW