የአዳማ ቆርቆሮ ፋብሪካ ከትንሽ ጀምሮ ወደ ትልቅነት የመድረስ ተምሳሌት ነው – ጠ/ሚ ዐቢይ

የካቲት 28/2014 (ዋልታ) የአዳማ ቆርቆሮ ፋብሪካ ከትንሽ ጀምሮ ወደ ትልቅነት የመድረስ ተምሳሌት ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ፡፡
ዛሬ የተመረቀው የማስፋፊያ ፕሮጀክቱ ኢንዱስትሪዎቻችን በሀገር ውስጥ አስፈላጊ የግንባታ ግብአቶችን ለማምረት ያላቸውን ከፍተኛ ዐቅም የሚያሳይ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጣቸው አስፍረዋል።
እንዲህ ያሉ ሀገር በቀል ሞዴሎችን ማበራከት የውጭ ምንዛሪ ወጪያችንን በእጅጉ ለመቀነስ ያስችላል ሲሉም አክለዋል።