የአፍሪካ ኅብረትን በሊቀመንበርነት የመሩት 19 መሪዎች እነማን ናቸው?

የአፍሪካ ኅብረት

የአፍሪካ አንድነት ድርጅትን በፈረንጆቹ 2002 የተካውን የአፍሪካ ኅብረት የተለያዩ ሀገራት መሪዎች በሊቀመንበርነት መርተውታል።

የአፍሪካ ኅብረት ሊቀመንበር የሚመረጠው የህብረቱ አባል ሀገራት ከመከሩበት በኋላ በአፍሪካ ህብረት ጠቅላላ ጉባኤ ነው።

የህብረቱ ሊቀመንበር ሆኖ የሚመረጠው የሀገራት ርዕሰ መንግስት ወይም ርዕሰ ብሔር  ሲሆን ለአንድ ዓመት የሚቆይ የአገልግሎት ዘመን ይኖረዋል።

በአሁኑ ወቅት የህብረቱ ሊቀመንበር ሆነው እየመሩ ያሉት የኮንጎ ዴሞክራሲያዊት ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ፌሊክስ አንቶኒ ትሺኬዲ ናቸው።

የአፍሪካ ህብረትን ከፈረንጆቹ 2002 ወዲህ በሊቀ መንበርነት የመሩት የሀገራት መሪዎች

ከሐምሌ 2002 እስከ ሐምሌ 2003 የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ታቦ ምቤኪ፣

ከሐምሌ 2003 እስከ ሐምሌ 2004 የሞዛምቢክ ፕሬዚዳንት ዮአኪም አልቤርቶ ቺሳኖ፣

ከሐምሌ 2004 እስከ ታህሳስ 2005 የናይጄሪያ ፕሬዚዳንት ኦሉሴጉን ኦባሳንጆ፣

ከጥር 2006 እስከ ጥር 2007 የኮንጎ ፕሬዚዳንት ዴኒስ ሳሱ ንግኤሶ፣

ከጥር 2007 እስከ ጥር 2008 የጋና ፕሬዚዳንት ጆን ኩፎር፣

ከጥር 2008 እስከ ጥር 2009 የታንዛኒያ ፕሬዚዳንት ጃካያ ምሪሾ ክክዌቴ፣

ከየካቲት 2009 እስከ ጥር 2010 የሊቢያ መሪ ሙአመር ጋዳፊ፣

ከጥር 2010 እስከ ጥር 2011 የማላዊ ፕሬዚዳንት ቢንጉ ዋ ሙታሪካ፣

ከጥር 2011 እስከ ጥር 2012 የኢኳቶሪያል ጊኒ ፕሬዚዳንት ቴኦዶሮ ቢያንግግ ንጉዌማ ምባሰጎ፣

ከጥር 2012 እስከ ጥር 2013 የቤኒን ፕሬዚዳንት ቶማስ ቦኒ ያዪ፣

ከጥር 2013 እስከ ጥር 2014 የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ፣

ከጥር 2014 እስከ ጥር 2015 የሞሪታኒያ ፕሬዚዳንት ሞሃመድ ኦውልድ አብደል አዚዝ፣

ከጥር 2015 እስከ ጥር 2016 የዚምባብዌ ፕሬዚዳንት ሮበርት ሙጋቤ፣

ከጥር 2016 እስከ ጥር 2017 የቻድ ፕሬዚዳንት ኢድሪስ ዴቢ፣

ከጥር 2017 እስከ ጥር 2018 የጊኒ ፕሬዚዳንት አልፋ ኮንዴ፣

ከጥር 2018 እስከ የካቲት 2019 የሩዋንዳ ፕሬዚዳንት ፖል ካጋሜ፣

ከጥር 2019 እስከ የካቲት 2020 የግብፅ ፕሬዚዳንት አብደል ፋታህ አልሲሲ፣

ከየካቲት 2020 እስከ የካቲት 2021 የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ እና

ከየካቲት 2021 እስከ የካቲት 2022 የዴሞክራሲያዊት ሪፐብሊክ ኮንጎ ፕሬዚዳንት ፌሊክስ አንቶኒ ሺሴኬዲ ናቸው።