የአፍሪካ የትምህርት ቤት ምገባ ቀን እየተከበረ ነው

የካቲት 21/2014 (ዋልታ) 7ኛው የአፍሪካ የትምህርት ቤት ምገባ ቀን ዛሬ እየተከበረ ነው።
ቀኑ “ለአገር በቀል የትምህርት ቤት ምገባ መርሃ ግብር የሚደረግ ኢንቨስትመንትን በመጨመር ሥርዓተ ምግብና የሰው ኃይል ልማትን ማሳደግ” በሚል መሪ ቃል እየተከበረ እንደሚገኝ የአፍሪካ ኅብረት አስታውቋል።

የምገባ ቀኑ የአፍሪካ አገራት በአገር በቀል የትምህርት ቤት ምገባ መርሃ ግብሮች የሰው ኃይል ልማት ለውጥ እንዲያመጡና የዘላቂ ልማት ግቦችን ለማሳካት ያላቸውን ቁርጠኝነት ዳግም እንደ አዲስ የሚያድሱበት እንደሆነ ኢዜአ ዘግቧል።

7ኛው የአፍሪካ የትምህርት ቤት ምገባ ቀን የአፍሪካ ኅብረት ከዓለም ምግብ ፕሮግራምና ከሌሎች የልማት አጋሮች ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ሲሆን ቀኑ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት በሚሳተፉበት የበይነ መረብ የፓናል ውይይት እንደሚከበር ተነግሯል።