የኢትዮጵያዊያንን የአሸናፊነት ታሪክ ማስቀጠል ይገባል – አፈጉባኤ ታገሰ ጫፎ

ጥቅምት 27/2014 (ዋልታ) የአገርን ሉኣላዊነት በማስጠበቅ የኢትዮጵያዊያንን የአሸናፊነት ታሪክ ማስቀጠል እንደሚገባ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ ገለፁ።

ምክር ቤቱ ለ6 ቀናት በአፍሪካ የአመራር ልህቀት አካዳሚ ሲያካሂድ የቆየውን የሥራ ማስጀመሪያ የምክክር እና የውይይት መድረክ አጠናቋል።

በመድረኩ ማጠናቀቂያ አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ የአገርን ሉኣላዊነት በማስጠበቅ የኢትዮጵያዊያንን የአሸናፊነት ታሪክ ማስቀጠል እንደሚገባ ተናግረዋል።

በቀደምት ጀግኖች አኩሪ ተጋድሎ ደምና አጥንት በጽኑ አለት ላይ የተገነባችው ኢትዮጵያ የተለያዩ ኃይሎች በሚፈጥሩት ውዥንብር የምትፈርስ አገር አይደለችም ብለዋል።

እንደ ኢዜአ ዘገባ ለአገር ሰላም፣ ደኅንነትና ሉኣላዊነት መጠበቅ ከሕዝብ የተሰጠን ኃላፊነት በብቃት መወጣት አለብንም ብለዋል።