የኢትዮጵያ ልኡካን ቡድን ለኅብረቱ ሥራ አስፈፃሚ ምክር ቤት ስብሰባ ሉሳካ ገቡ

ሐምሌ 7/2014 (ዋልታ) በኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የተመራ ከፍተኛ የልኡካን ቡድን ለአፍሪካ ኅብረት 41ኛ ሥራ አስፈፃሚ ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ላይ ለመካፈል ዛምቢያ ዋና ከተማ ሉሳካ ገቡ።

ምክር ቤቱ ከዛሬ ጀምሮ ስብሰባውን ለሁለት ቀናት የሚያካሂድ ሲሆን በስብሰባው የአጀንዳ 2063 የመጀመሪያ አስር ዓመታት አፈፃፀምን እንደሚገመግምና በቀጣዩ 10 ዓመታት ዕቅድ ላይም እንደሚወያይ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ከዚህ በተጨማሪ የኅብረቱ አባል ሀገራት መሪዎች በሥነ ምግብ ዘርፍ በግማሽ ምንተ ዓመቱ ስለሚፈፀሙ ተግባራት እንደሚወያዩም ተመላክቷል።

በስብሰባው ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተጨማሪ ቀድሞ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ እንደሚሳተፉ ታውቋል፡፡

የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ በአፍሪካ የግብርና ዘርፉን ለማዘመን የተቋቋመው አግራ የተሰኘው ተቋም የቦርድ ሰብሳቢ መሆናቸው ይታወቃል፡፡ ተቋሙና መስሪያ ቤቱን ኬኒያ ዋና ከተማ ናይሮቢ አድርጎ በተለያዩ የአኅጉሪቷ ሀገራት እንደሚሰራም ይታወቃል፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW