የኢትዮጵያ ቡና የኢትዮጵያ ዋንጫ ሻምፒዮን ሆነ

ሰኔ 30/2016 (አዲስ ዋልታ) በአዲስ አበባ ስታዲየም የተከናወነው የ2016 የኢትዮጵያ ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታ በቡናማዎቹ አሸናፊነት ተጠናቋል።

መደበኛ የጨዋታ ክፍለ ግዜው አበባየሁ ሀጂሶ ለወላይታ ድቻ እንዲሁም ዋሳዋ ጂኦፍሪ ለኢትዮጵያ ቡና ባስቆጠሩት ግብ አንድ አቻ ተጠናቋል።

ወደ ጭማሪ ሰዓት ያመራውና ብርቱ ፍክክርን ያስተናገደው ይህ ጨዋታ 116ኛው ደቂቃ ላይ በድጋሚ የኢትዮጵያ ቡና ዋሳዋ ጂኦፍሪ ባስቆጠረው ፍፁም ቅጣት ግብ አማካኝነት የጨዋታው አሸናፊ ሁነዋል።

ኢትዮጵያ ቡና ለስድስተኛ ጊዜ የኢትዮጵያ ዋንጫን ማሸነፍን ተከትሎ በቀጣይ የውድድር ዓመት በአፍሪካ ክለቦች ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ኢትዮጵያን ይወክላል።

የአዲስ አበባ ስታዲየም ከሦስት ዓመት ገደማ በኋላ በክለቦች መካከል የተከናወነ ታላቅ የፍፃሜ ጨዋታ አስተናግዷል።

የሁለቱ ቡድን ደጋፊዎችም የእለቱ ጨዋታ ልዩ ድምቀት ሁነው ታይተዋል።

በቀጣይ የዉድድር ዓመት ንግድ ባንክ በአፍሪካ ክለቦች ቻምፒየንስ ሊግ የኢትዮጵያ ቡና በአፍሪካ ክለቦች ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ዉድድር ኢትዮጵያን የሚወክሉ ቡድኖች ናቸው።

በሀብታሙ ገደቤ