የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ለአምስት ባንክ ላልሆኑ የውጭ ምንዛሪ ቢሮዎች የስራ ፈቃድ ሰጠ

መስከረም 22/2017 (አዲስ ዋልታ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ለአምስት ባንክ ላልሆኑ የውጭ ምንዛሪ ቢሮዎች የስራ ፈቃድ መስጠቱን አስታቀወቀ።

ባንኩ ዱግዳ ፊደሊቲ ኢንቨስትመንት ፒኤልሲ፣ ኢትዮ ኢንድፔንደንት ፎሬይን ኤክስቼንጅ ቢሮ፣ ግሎባል ኢንድፔንደንት ፎሬይን ኤክስቼንጅ ቢሮ፣ ሮበስት ኢንድፔንደንት ፎሬይን ኤክስቼንጅ ቢሮ እና ዮጋ ፎሬእስ ለተባሉ ባንክ ላልሆኑ የውጭ ምንዛሪ ቢሮዎች ነው ፈቃዱን የሰጠው።

ቢሮዎቹ ተቀባይነት ያላቸውን የውጭ ሀገር ጥሬ ገንዘቦችን በመግዛትና በመሸጥ እንዲሁም ከባንኮች ጋር በመቀናጀት ለወጭና ገቢ ንግድ የሚውል የውጭ ምንዛሪ የማመቻቸት ሚና እንደሚኖራቸው ባንኩ አስታውቋል።

የውጭ ምንዛሪ ቢሮዎቹ ያለ ዲክላራሲዮን ከደንበኞች እስከ 10 ሺህ የአሜሪካን ዶላር እንዲሁም የጉምሩክ ፈቃድ ከሚያቀርቡ ደግሞ ከዛ በላይ የውጭ ምንዛሬ በጥሬ ገንዘብ መግዛት እንደሚችሉም ባንኩ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባወጣው መረጃ ጠቁሟል።

ብሔራዊ ባንክ ያወጣቸውን ደንቦች፣ አሰራሮች የደህንነት ሪፖርት አደራረግ መዝገብ አያያዝ መስፈርቶችን በተገቢ ሁኔታ ተግባራዊ ማደረግ አለማድረጋቸውን በጥብቅ ቁጥጥርና ክትትል እንደሚያደርግ አስታውቋል።